ፓሪስ ከሽብር ጥቃቱ በኋላ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 30 2007ማስታወቂያ
የፓሪስ ነዋሪዎችም ድርጊቱን በመቃወም ትናንት ምሽት በአደባባይ በነቂስ ወጥተዋል። ፈረንሳይ የትናንቱን የአሸባሪ ቅጣት ተከትሎ ፈረንሳይ ብሔራዊ የሃዘን ቀን ማወጅዋ ይታወቃል። በሌላ በኩል አንድ ሴት ፖሊስም ከየት መድረሱ ባልታወቀ ጥቃት መገደልዋ እንዲሁም ሁለት በፅኑ መቁሰላቸዉ ተነግሮአል። ዛሬ ፓሪስ እንዴት ዉላ ይሆን? ሌላ አንድ ፖሊስ የመገደልዋ ዜናስ እንዴት ነዉ? የፓሪስዋን ወኪላችንን ሐይማኖት ጥሩነህን አነጋግረናታል።
ሐይማኖት ጥሩነህን
አዜብ ታደሰ