ፈረንሳይ ወታደራዊ ስምምነቱን ስለማገዷ አስተያየት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 12 2013ማስታወቂያ
ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችዉን ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ማገዷን ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። እንደዘገባው ከኾነ መጋቢት 2019 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ መካከል የተደረሰዉ ስምምነት ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ታግዷል። ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የመገንባት ፍላጎቷን ለመደገፍ ፈረንሳይ 85 ሚሊዮን ዩሮ (100 ሚሊዮን ዶላር) ብድርን የምትሰጥበት ስምምነት በሁለቱ ሃገራት መካከል ተፈጽሞ እንደነበርም ተዘግቧል። ፈረንሳይ የወሰደችው አቋም አንድምታው እንዴት ይታያል፤ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወዴት አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ የፈረንሳይ ምሑራን እና የቀድሞ የፈረንሳይ ዲፕሎማት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ