ፈረንሳይ በሲንቲዎች ላይ የጀመረችው ዘመቻ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 18 2002ማስታወቂያ
ተንቀሳቃሽ ህዝቦች ናቸው ። ከአያት ቅደመ አያቶቻቸው ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው ከዚህ ልምዳቸው ዛሬም አልተላቀቁም ። በተለያዩ የአውሮፓ ሐገራት ውስጥ ለዘመናት ቢኖሩም ከዘመነው አውሮፓ ጋር የሚመሳሰል ህይወት ግን የላቸውም ። የአብዛኛዎቹ ኑሮ ከ3ተኛው ዓለም ድሀ ህዝብ ጋር ይቀራረባል ። በየሚኖሩበት ሐገር የተገለለ ህይወት የሚገፉት እነዚህ ህዝቦች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ከአንዳንድ የምዕራብ አውሮፓ ሐገራት በግዳጅ እየተባረሩ ነው ። በቅርቡ ይህን መሰሉን ዕርምጃ በይፋ ከወሰዱት አገራት ውስጥ አንዷ ፈረንሳይ ናት ። ፈረንሳይ ባለፈው ሳምንት ህገ ወጥ ያለቻቸውን ሲንቲ ሮማዎች ወደ ሩሜንያ አባራለች ። ይህ የፈረንሳይ ዕርምጃም ከየአቅጣጫው ተወግዟል ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የአውሮፓ ህብረት ጭምር የፈረንሳይን መንግስት ድርጊት ተችተዋል ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ