እየጎዱት የሚገኘዉ ህዝብ ቁጥር ሲታይ ማለት ነዉ። ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋ የሚኖሩ ወገኖች በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸዉ መጨመሩ ይነገራል። ዋነኛ ምክንያቱም በሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ተጠቅተዉ ይሞቱ የነበሩት ወገኖች በሽታ የመቋቋም አቅማቸዉ እንዲጠናከር የሚረዱ መድሃኒቶች በስፋት መዳረስና ለሰዎችም በነፃ የማደሉ ተግባር እየተስፋፋ መሄዱ ነዉ። መድሃኒቱ ከስያሜዉ አንስቶ ማነጋገሩ አልቀርም። ዋንኛ ጥቅሙስ ምን ይሆን?