ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ጥር 10 2005ማስታወቂያ
ጥምረት ለህይወት ኢትዮጵያ በብዛት ከውጭ ሀገር በሚገኝ ድጎማ ይንቀሳቀሳል።
ድርጅቱ ከተመሰረተ ስምንት አመት ሊሆነው ነው። በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በርካታ ሴቶችን ሰብስቦ በሙያ ያሰለጥናል። አቶ ተፈራ አለሙ፤ የፕሮግራም አስተባባሪ እንዲሁም ድርጅቱን ከመሰረቱት አንዱ ናቸው። ስለድርጅቱ አላማ አጫውተውናል።
እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በስልጠና ላይ የሚገኙት መሰረት በቀለ እና በቀለች ደበሌም ስለ ስልጠናቸው ገልፀውልናል። ለሰልጣኞቹ የወደፊት የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ከሚጥሩት አንዱና የስልጠና ክፍል ኃላፊ የሆነው መስፍን ክፍሌ የበኩሉን ብሎናል።
ከዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ