አደገኛ የወፍ ጉንፋን በቻይና መልኩን ቀይሮ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ ነው ተብሏል። ገዳዩ የኢቦላ ቫይረስ ከኮንጎ ወደ ጎረቤት አገር አንጎላ እንዳይገባ ተሰግቷል። ኤድስን አስመልክቶ በአፍሪቃ መጠነኛ መሻሻል መታየቱና፤ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የሂሮሺማና ናጋሳኪ የአቶሚክ ቦንብ ጥፋት የጨረር ጉዳተኛ አዛውንት ኮሪያውያን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ቅኝት ይኖረናል፤ በዛሬው የጤናና አካባቢ ጥበቃ ዝግጅታችን።