ጠፉ የተባሉት የኮንደሚኒየም ሕንጻዎች
ሰኞ፣ ግንቦት 8 2008ማስታወቂያ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቤቶችና የከተማ ልማት ሚኒስቴር የሥራ አፈፃፀም ዝርዝር ዘገባ ባደመጠበት ወቅት ጠፉ እየተባለ ስለሚነገርላቸዉ የኮንደሚኒየም ቤቶች የሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ አጣርቶ እንዲያቀርብ መጠየቁ ተሰምቷል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ታቅደዉ ያልተሠሩ መኖራቸዉን ለምክር ቤቱ ቢጠቁምም፤ ጠፋ የተባሎት የኮንደሚኒየም ቤቶች ጉዳይ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ገጾች የመነጋገርያ ርእስ ሆኗል። ጉዳዩን ጠቅሶ የአዲስ አበባ የቤቶችና የልማት አስተዳደር ቢሮን ያነጋገረዉ የአዲስ አበባዉ ዘጋብያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የሰመጠም፣ የተሰወረም ሕንፃ እንደሌለ መስሪያ ቤቱ መግለጹን በላከልን ዘገባ ጠቅሶአል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ