ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወስዷቸው ርምጃዎች አንድምታ
እሑድ፣ ግንቦት 19 2010ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መግባባት እንዲሰፍንባት በሚሞክሩባት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በምትገኘው ሀገር አሁንም የሰዎች መፈናቀል፤ የሕይወት መጥፋት እና ጉዳት ዜና እንደሆነ ቀጥሏል። አዲስ ራዕይ ይዘው መነሳታቸውን የሚገልፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል።
ግን ደግሞ ራዕይ ጥረታቸው እንዲሳካ የገለልተኛ ተቋማት ነገር ቅድሚያ ቢሰጠዉ ያሳስባሉ። ባለፉት ሳምንታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያከናወኗቸው እንቅስቃሴዎችና ርምጃዎች ተስፋ ሰጪዎች ቢሆኑም አዲስ ራዕይ እና አስተሳሰብ ያሉትን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ግን ፈተናዎች ሊደቀኑ እንደሚችሉ ግምት የሚሰነዝሩም አልጠፉም። ዶይቼ ቬለ በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚወሰዱ ርምጃዎች አንድምታ ላይ ውይይት አካሂዷል።
ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ