1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎበዙ ተማሪ

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2011

ትምህርቱን የተማረው የወ/ሮ አየለች ደገፉ መታሰቢያ አፀደ ህፃናትና አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ሙሉሳይክል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ብሩክ ዘውዱ በትምህርት ቤቱ ቆይታው ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከልም ነበር። ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ አንደኛ እየወጣ ነዉ ያጠናቀቀዉ።

https://p.dw.com/p/3ON1M
Brook Zewdu Schüler Äthiopien
ምስል DW/A. Mekonnen

ጎበዙ ተማሪ

ትምህርቱን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ የተማረው የአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ሀብት በሆነውና በእናቱ ስም በተሰየመው የወ/ሮ አየለች ደገፉ መታሰቢያ አፀደ ህፃናትና አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ሙሉሳይክል ትምህርት ቤት ነው፡፡ ብሩክ ዘውዱ በትምህርት ቤቱ ቆይታው ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከል አንዱ እንደነበርና ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ አንደኛ እየወጣ ማጠናቀቁን ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል፡፡ የ2011 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው ውጤት ከሚጠብቁት ተማሪዎች መካከልም ከአቶ ዘውዱ ባይሌና ከወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጥላሁን ከ19 ዓመታት በፊት የተወለደው ብሩክ ዘውዱ ያመጣውን ውጤት ለማወቅ ከኮምፒዩተር ቤት ወደ ኮምፒዩተር ቤት እየተዘዋወረ ሲሞክር የኔት ወርክ ችግር በማጋጠሙ ቶሎ ማወቅአልቻለም ነበር፡፡ ከጓደኛው ቤት በመሄድና  ያመጣውን  ውጤት ከአገር አቀፉ የትምህርት ምዘናናፈተናዎች ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ ማወቅ እንደቻለ ይናገራል፡፡ ሆኖም ከፍተኛው ውጤት መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂ ፈተና ከፍተኛው ውጤት 645 መሆኑንና በአማራ ክልል መመዝገቡ ከገለፀ በኋላ ግን የውጤት ባለቤት ብሩክ ራሱ መሆኑን ማረጋገጡን በደስታ ተናግሯል፡፡ የብሩክ ዘውዱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጥላሁን ብሩክ  ከልጅነቱ ጀምሮ የተለየ ባሕሪ እንደነበረው የፈለገው ነገር ካልተሰጠው እስከመጨረሻ ጠይቆ ያገኝ ነበር ብለዋል፡፡ በቤት ውስጥም  አሁን የህክምና ትምህርቷን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምትማረው ታላቅ እህቱ ማህሌት ዘውዱ ጋር በመሆን እናቱን በተለያየ መንገድ እግዛ ያደርግ  እንደነበር በተለይም በወንዶች ብዙ ያልተለመደውን ሊጥ አቡክቶ ኬኬና ዳቦ ይጋግረም  እንደነበር ወ/ሮ ኤልሳቤጥ በቆይታችን ወቅት አቻዉተውኛል፡፡ ከ9 ዓመት በፊት የስዕል ባለሙያ የነበረውን ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ከዚያ በኋላ ህይወት ፈተና ቢሆንም  ዶርሞችን በማከራት፡ እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ ተግተው በመስራትና  እናታቸው ጠላ በመሸጥ እደጎሟቸው ልጆቻቸውን ለዛሬው ደረጃ እንዳደረሷቸው አመልክተዋል፡፡ ብሩክ ታላቅ ወንደድም ኃይሌ ዘውዱ እንደሚለው “አይዞህ በርታ” ከማለት ውጭ ብዙም ድጋፍ እንዳላደረገለት አመልክቶ “ሁሉም በእናታችን ድጋፍ ነው፣ ምስጋናውም ለሷመሆን አለበት” ብሏል፡፡ ብሩክ ወደፊት የውጭ አገርየትምህርት እድል ካገኘ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ በአገር ውስጥ ከሆነ ደግሞ ህክምና የማጥናት ፍላጎት እንዳለው ገልፆልናል፡፡ በመጨረሻም በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ  አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውን ባለሀብቶች ና ባለድርሻ አካላት ብሩክ የተሻለ ትምህርት እንዲገኝ እገዛ እንዲደርጉለት ቤተሰቦቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በ2011 ዓም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥር 320 ሺህ ይጠጋል፡፡

ዓለምነው መኮንን 
አዜብ ታደሰ