1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎርፍ ያስከተለዉ ቀዉስ በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2008

በኤል ኒኞ ሳቢያ ባለፉት 50 ዓመታት ዉስጥ ተከስቶ የማያቅ ድርቅ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመከሰቱ ከ10,2 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለምግብ እጥረት ቀዉስ መዳረጉ ይታወቃል። ይህን ለመቋቋም የኢትዮጵያ መንግሥት 1,4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገዉ አሳዉቆ ርዳታ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/1IpGz
Karte Äthiopien englisch

[No title]

ይህ ሆኖ እያለ፣ ለወራት ጠፍቶ የነበረዉ ዝናብ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፣ ማለትም በሶማሊያ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በሐረር እና በደቡብ ብሄር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ በከፍተኛ መጠን በመጣሉ በጎርፍ አደጋ 120,000 ሰዎች ከመኖሪያ ቦታቸዉ አፈናቅሏል። ከለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ወደ 100 ሰዎች መሞታቸዉንም መንግሥት እና የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ይናገራሉ።


ከዝናብ ጋር ተያይዞ የቅድመ ማስጠንቀቅያ ሥራዎችን መረጃ በማቀበል እየሠራን ነዉ የሚሉት በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘዉዴ አደጋዉ ከመድረሱ በፊት ቦታዉን እንዲለቁ እያደረጉ መሆናቸዉንም ገልጸዋል። ቦታዉን ለቀዉ ሲሄዱም ኮሚሽኑ ምግብ እና መጠልያ እየስጠ እንደሚገኝ እና ቀዉሱን ለመቋቋምም ከተለያዩ የፌደራል ተቋሞች ጋር እየሠሩ መሆናቸዉን ያብራራሉ።



የዝናቡ ሁኔታ መጨመሩን አቶ ደበበ ከተናገሩ በኋላ በወንዞች አካባቢ ያለዉ ኅብረተሰብ፣ ለምሳሌ በገናሌ፣ በዳዋ፣ በአዋሽ፣ በዋቢ ሸበሌ እና በጣና ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃ እያደረሰን ነዉ በማለትለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይሄን አደጋ የሚከታተል ግብረ ኃይል ተቋቁሟል የሚሉት አቶ ደበበ <<ድርቁ ያልጎዳንን ያህል ጎርፉ በሰዉ ሕይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ>> የተጠናከረ ክትትል በማድርግ ላይ እንደሚገኙም ዘርዝረዋል።

Tanasee in Äthiopien
ምስል picture alliance/Peter Groenendijk/Robert Harding


የጎርፍ ፍሰት በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊጨምር እንደሚችል ስታርት ኔትዎርክ የተሰኘዉ የአደጋ ሁኔታዎች ላይ መረጃ የሚያቀብል ተቋም ከወዲሁ ጠቁሟል። ከቦታቸዉ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥርም በዚህ ወር ወደ 189, 660 ሊደርስ እንደሚችል እና 485, 600 ሰዎችም በጎርፍ ለጠቁ እንደሚችሉ ዘገባዉ ያሳያል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ