ግጭቶችና የፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር፣ 30 ግንቦት 2004ሐሙስ፣ ግንቦት 30 2004ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ ብሔር -ብሔረሰብንና ቋንቋን መሠረት ማድረጉ የሚነገርለት የፌደራል ሥርዓት፣ ችግሮችን እንዳላስወገደ ሲነገር ቆይቷል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች አምባጓሮም ሆነ ግጭትhttps://p.dw.com/p/15AJyምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ በየጊዜው መፈጠራቸው በመገናኛ ብዙኀን ሲገለጥ የቆየ ጉዳይ ነው። በቅርቡም፤ ባለፈው እሁድ፤ በአፋር መስተዳድር፤ በአፋሮችና ኢሳዎች መካከል በተካሄደ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውና 6 መቁሰላቸውን የጠቀሰልን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር መፍትኄ በመሻቱ ረገድ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር ምን እያደረገ እንደሆነ ጠይቆ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ ሸዋዬ ለገሰ