1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግዕዝ ፊደል በዘመነ ኮምፒዩተር

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 19 2004

ያለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን፤ ዘመነ መረጃ፣ ዘመነ ኮምፒዩተር መባሉ ያለምክንያት አይደለም::

https://p.dw.com/p/13bZu
ምስል picture-alliance / M.i.S.-Sportpressefoto

መረጃ እንደልብ የሚሰራጭበት፤ የሰው ልጅ የደረሰበት እውቀት ለፈለገ ሁሉ በተፈለገ ግዜ የሚገኝበት መሆኑ ከከዚህ ቀደምቱ ዘመናት ስለሚለየው እንጂ:: በበለጸጉት ሀገራት በተለይ ኮምፒዩተር የማይገባበት የህይወት ዘርፍ የለምና፤ ያለኮምፒዩተር መኖር አዳጋች እሚመስልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል:: በመልማት ላይ ያሉ ሀገሮች ግን፤ በኢኮኖሚ አልያም በትምህርት ኋላ በመቅረት፣ የዚህ ዕድል ሙሉ ተጠቃሚ አይደሉም:: ኢትዮጵያ አንዷ ናት:: የራሷ ብቻ የሆነ የግዕዝ ፊደል ባለቤት መሆኗ ደግሞ ተጨማሪ ፈተና አለው::ባለፉት 25 አመታት፣ ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የሚያጋለገልውን የጋራ ቅርሳችንን ፣ ግዕዝን በኮምፒዩተር መክተብ ከመጀመሩ በፊት፤ ፊደሉ የሚጻፈው በእጅ ወይም በማተሚያ ቤቶች ብቻ ነበር:: አሁን- አሁን ግን፤ የግዕዝ ፊደል ከኢንተርኔት መጠቀሚያ ቋንቋዎች ጎራ ገብቷል:: ያሁ፣ ጉግል እና ቢንግ በመባል በሚታወቁ የኢንተርኔት መረጃ መፈለጊያዎች ግዕዝን ካወቁት ሰንብቷል:: ማይክሮሶፍት በመባል የሚታወቀው ትልቁ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ደግሞ በቅርቡ በአማርኛ መጠቀም የሚያስችል አሰራር አካቷል::

ንግሥት ሰልፉ፤

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ