ግብረ ሠዶማዉያንና የቂርቆስ ወጣቶች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2005ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዉስጥ የቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ወጣቶች በአካባቢያቸዉ የግብረ-ሰዶማዉነት መስፋፋትን ለመገድብ እንደሚጥሩ አስታወቁ።የወጣቶቹ ማሕበር በጠራዉ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የሕክምና ባለሙያዎችና የሐይማኖት መሪዎችም ግብረ-ሰዶማይነትን ያስፋፋሉ ባሏቸዉ ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ጠይቀዋል።ገነት ሆቴል በተዘጋጀዉ ዉይይት ላይ ከሁለት ሺሕ የሚበልጡ ወጣቶች፥የሐይማኖት ተጠሪዎች እና በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ጥናት ያደረጉ ምሑራን ተካፍለዉ ነበር።ጌታቸዉ ተድለ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድለ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ