ጋሊፖሊ-900 ስደተኞቹ ከሞት ለጥቂት ዳኑ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2007ማስታወቂያ
የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር በአንድ መርከብ ተሳፍረዉ የነበሩ ዘጠኝ መቶ ሥደተኞችን ከሞት አፋፋ ማዳኑንን አስታወቀ።የጦሩ አዛዦች እንዳስታወቁት ስደተኞቹን አሳፍራ ወደ ኢጣሊያ ባሕር ጠረፍ ትቀዝፍ የነበረችዉ መርከብ ሞተር ድንገት «በመንከሱ» መርከቢቱ ባሕሩ ጠረፍ ከሚገኝ አለታማ ተራራ ጋር ልትጋጭ ጥቂት ኪሎሜትር ነበር የቀራት።አኩለ ሌሊት ግድም የተሳፋሪዎቹ የርዳታ ጥሪ የደረሳቸዉ የባሕር ሐይል ባልደረቦች ከሔሊኮፕተር መርከቢቱ ላይ ወርደዉ ሞተሩን አላቀዉ፤ የመርከቢቱን አቅጣጫ ማስቀየር ችለዋል።የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፖ ማሪኒ እንደሚሉት ባልደረቦቻቸዉ ባይደርሱ ኖሮ ዓለም በሌላ የባሕር ላይ ጥፋት ባዘነ ነበር።አብዛኞቹ ስደተኞች የሶሪያ ዜጎች ናቸዉ።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ