ጉማሬዎች ሞቱ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2011ማስታወቂያ
ደቡብ ክልል ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙ ጉማሬዎች ባልታወቀ ምክንያት እየሞቱ እንደሆነ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ጠቆመ። የቢሮ ኃላፊዎች እንዳሉት ፓርኩን አቋርጦ በሚያልፈዉ የጊቤ ወንዝ ዳርቻ ላይ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የ28 ጉማሬዎች አስከሬን ተገኝቷል። ከደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከፌደራል የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በስፍራው ደርሶ ጉማሬዎቹ የሚሞቱበትን ምክንያት እየመረመረ ነዉ።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም ወልደየስ