ጆ ባይደን በባልካን
ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሶስት ቀናት የባልካን ሀገራት ጉብኝት ሰርቢያ ይገኛሉ። በጉብኝታቸውም፤ ሰርቢያ ነፃ ለሆነችው የቀድሞ ግዛቷ ኮሶቮ እውቅና እንድትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ አትጠብቅም ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። ለኮሶቮ ከሰርቢያ መገንጠል ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች ሲታወቅ፤ ለአዲሲቷ ሀገር ኮሶቮም እውቅና በፍጥነት ነበር የሰጠችው። የጆ ባይደን የጉብኝት ዓላማ በባልካን አካባቢ መረጋጋት እንዲፈጠር መጣር እንደሆነም ተገልጿል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ