ጅቡቲ ደርሶ መልስ-ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2010ማስታወቂያ
ከጅጅጋ እስከ መቀሌ ከአምቦ እስከ ባሕር ዳር ተከታታይ ጉዞዎች እና የምክክር መድረኮች ላይ የከረሙት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ የመጀመሪያ የውጭ አገር ጉብኝታቸውን አድርገዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ወደ ጅቡቲ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌሕ እና ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት ጋር ውይይት አድርገዋል። በጅቡቲ ቆይታቸው ወደቦች ጭምር ጎብኝተዋል። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተውም ንግግር አድርገዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መለስ አለምን በማነጋገር የሚከተለውን ዘገባ አድርሶናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ