ጄኮብ ዙማ1 ግንቦት 2001ቅዳሜ፣ ግንቦት 1 2001አዲሱ የደቡብ አፍሪቃ ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አድርጎ የመረጣቸወ የአፍሪቃውያኑን ብሄረተኞች እንቅስቃሴ ኤ ኤን ሲ መሪ ጄኮብ ዙማ ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ።https://p.dw.com/p/HmO3ምስል APማስታወቂያከ አራት መቶ የምክር ቤት እንደራሴዎች መካከል የሁለት መቶ ሰባ ሰባቱን ድምጽ ያገኙት ዙማ በነገው ዕለት ካቢኔአቸውን ይፋ ያደርጋሉ። ይህ ደቡብ አፍሪቃ ወደፊት የምትከተለውን ፖሊሲ የሚጠቁም በመሆኑ ብዙዎች በስጋት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ዙማ በሀገሪቱ የዘር አድልዎ አመራር ከተገረሰሰ በህዋላ ለአራተኛ ጊዜ የተመረጠው ዴሞክራሲያዊ መንግስት አመራርን ነው ዛሬ የተረከቡት። LS/AA/RTR