ጁባ-የደቡብ ሱዳን ሹም ሽርና ሥጋቱ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 19 2008ማስታወቂያ
ፕሬዝደንት ኪር ባለፈዉ ነሐሴ በተፈረመዉ የሠላም ሥምምነት መሠረት የተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደትነቱን ሥልጣን የያዙትን የተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቸርን ሽረዉ የቀድሞዉን የአማፂ ቡድን ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይን ዛሬ ሾመዋል።
ታባን ዴንግ ጋይ በቅርቡ በተሰየመዉ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ዉስጥ የማዕድን ሚንስትር ነበሩ።ኪር ዋናዉን የአማፂ ቡድን መሪ ማቸርን ሽረዉ ታባን ዴንግ ጋይን የሾሙት ማቸር በቅርቡ ጁባ ዉስጥ ከተቀሰቀሰዉ ግጭት በኋላ ተሰዉረዋል በሚል ሰበብ ነዉ።ታባን የቀድሞ አለቃቸዉን ክደዉ ሹመቱን መቀበላቸዉን «በማቸር መሰወር ምክንያት የተፈጠረዉን ክፍተት ለመሙላት ይረዳል በማለት አስታዉቀዋል።ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን የጦር ጄኔራሎችና ሚሊሻዎች አሁንም የማቻር ታማኞች በመሆናቸዉ ሹም-ሽሩ የከፋ ደም መፋሰስ ያስከትላል የሚል ሥጋት አሳድሯል።
ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በደቡብ ሱዳን ለሦስት ቀናት በዘለቀዉ ጦርነት ወደ 300 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ 37 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት ዩጋንዳ ሸሽተዋል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በሬክ ማቻር ምትክ አዲስ ስለሰየሙት ምክትል ፕሬዚዳንት ናይሮቢ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይነዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ