ጀርመን እና የቀኝ አክራሪዎች የግድያ ወንጀል
ሰኞ፣ ኅዳር 4 2004ማስታወቂያ
የፍትኅ ሚንስትርዋ ወ/ሮ ዛቢነ ሎይቶይሰር -ሽናረንበርገርም ፣ የህገ-መንግሥት ጠባቂው ክፍል አሠራር፣ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር እስከማሳሰብ ደርሰዋል። ጀርመን ውስጥ የቀኝ አክራሪዎች፣ እ ጎ አ ከ 1990 ዓ ም፤ አንስቶ ከ 100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ገድለዋል። 16,000 ገደማ የሚሆን የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል። በተከታታይ ስለተፈጸሙ ግድያዎች ህዝብ ፤ የህግ አካላትና ፖለቲከኞች በጥሞና መነጋገራችው አልቀረም። በእርግጥ ምን እየተባለ ነው? ወደ እስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ፣ የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር። በእርሱ መልስ እንጀምራለን።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ