ጀርመንና የአቶም ሐይል ማመንጫዎችዋ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2003ማስታወቂያ
ጉዱዩ የአቶም ኃይል ማመንጫ ማዕካላቷን ዕድሜ ለማራዘም በወሰነችው በጀርመን በእጅጉ እያከራከረ ነው ። የጀርመንን የኒዩክለር ኃይል ማመንጫዎችን ለመዝጋት ከዚህ ቀደም የተያዘው ዕቅድ መቀልበስ የለበትም ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞአቸውን አሁን ይበልጥ እያስተጋቡ ነው ። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልም ሳይቀደሙ ፣ እጎአ በ 2010በመስከረም ወር የተላለፈውን የአቶም
ኃይል ማዕከላት መክሰሚያ ጊዜ ማራዘሚያ ውሳኔ እንደገና እንደሚጠና አስታውቀዋል ። በዚህ ምክንያትም ቢያንስ ሰባት አሮጌ የአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮች ለጊዜው እንዲዘጉ ተደርጓል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን በፉኩሽማው የአቶም ኃይል ማመንጫ ላይ በደረሰው ጉዳት መንስኤ ጀርመን ውስጥ የተነሳውን ክርክርና መንግስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ይመለከታል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሸ መሐመድ