ጀርመንና የምርጫ ዝግጅት፣
ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2005ማስታወቂያ
ተጣማሪ ፓርቲዎች CDU/CSU እና FDP እጩ ተወዳዳሪ አሁንም ራሳቸው መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሲሆኑ፣ ከዋናው ጠንካራ የተቃውሞ ፓርቲ (SPD)የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ፔር እሽታይንብሩክ መሆናቸው የታወቀ ነው።
ከታላላቆቹ ፓርቲዎች ሌላ ድምፅ የሚሻሙ ፤ የሥልጣኑን ሚዛን ይበልጥ ለአንዱ ወገን እንዲደፋ የሚያደርጉ አዳዲስ ፓርቲዎች በየጊዜው ብቅ ማለት ይዘዋል። አማራጭ ፈለግ እከታላለሁ የሚለውና ፣ ጀርመን ከዩውሮ ማኅበር እንድትወጣ ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሣው ፓርቲ ነው። ስለ ፓርቲዎች አሰላለፍና ስለምርጫ ዝግጅት የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።
ይልማ ኃ/ሚካኤል
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ