ጀሃዳዊ ሃረካት ዘጋቢ ፊልምና ተቃዉሞው
ሐሙስ፣ ጥር 30 2005ማስታወቂያ
በ29ኙ ተከሳሾች ላይ የሚቀርበዉን ምስክርነት በዝግ የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት የተባለዉ ፊልም እንዳይታይ ማገዱንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። እንዲያም ሆኖ ዘጋቢዉ ፊልም መታየቱ አልቀረም። የዘጋቢ ፊልሙ መቅረብ የሙስሊሙን ጥያቄ ሊያዳፍን አይችልም ሲል አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ መግለጫ አዉጥቷል፤ የተከሳሾች ጠበቆች አቤት ባሉት መሰረትም ፍርድ ቤት ለነገ ጉዳዩን እንደሚያይ ተሰምቷል። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን በዚህ ጉዳይ ላይ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በአጭሩ አነጋግሬዋለሁ።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ