ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በጸሐፊ፤ በጋዜጠኛ እና በአምባሳደር ዕይታ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 19 2011ማስታወቂያ
የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመን ፍራንክፉርት ከተማ ውስጥ ከሐሙስ ጀምሮ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ጠዋት 4 ሰአት ላይ ዛክሰን ሐውስ ሆስፒታል ውስጥ አርፈዋል። ፍራንክፉርት ኡኒቨርሲቴት ክሊንኒክ ውስጥ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ሲታከሙ የቆዩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ያረፉት በ76 ዓመታቸው ነው። ስለ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሕይወት ታሪካቸውን ከጻፈ፤ በሥራ ዓለም በቅርበት ካያቸው እና ጀርመን ፍራንክፉርት ከተማ ዛሬ ባረፉበት ሐኪም ቤት ተገኝተው ከነበሩ፤ ጸሐፊ፤ ጋዜጠኛ እና አምባሰድር ጋር የተደረጉት ቃለ መጠይቆች ከታች ድምጽ ማጫወቻዎቹ ውስጥ ይገኛሉ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ