ዶክተር አምባቸው መኮንን ተሾሙ
ቅዳሜ፣ የካቲት 30 2011ማስታወቂያ
ዶክተር አምባቸው መኮንን በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ። የአማራ ክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባዔ ክልሉን ሲመሩ የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ ዛሬ በምትካቸው ዶክተር አምባቸውን በርዕሰ መስተዳድርነት ሾሟል። ተሰናባቹ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር የአማራ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር የቆየውን ትስስር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችም እንዲቆሙ ጠይቀዋል። አለምነው መኮንን ከባህርዳር ዝርዝሩን ልኮልናል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ