ዶክተር መረራ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 20 2009ማስታወቂያ
በዛሬዉ ዕለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ የቀጠሮ ችሎት የቀረቡት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ፕሬዝደንት እና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸዉ። ከጠበቆቻቸዉም ሆነ ከራሳቸዉ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም መርማሪዎች የጀመርነዉ ምርመራ አልተጠናቀቀም በማለታቸዉ ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር 18 ቀጠሮ እንደሰጣቸዉ በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ገልፆልናል። ስለፍርድ ቤት ዉሎዉ አዜብ ታደሰ ዮሐንስን ቀደም ብላ በስልክ አነጋግራዋለች።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ