ድሪምላይነር አውሮፕላን በረራ መጀመሩ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2005ማስታወቂያ
ድሪም ላይነር ቦይንግ 787 ግዙፍ አውሮፕላን ገጠመው በተባለው የባትሪ ችግር ምክንያት ነበር ከመሬት እንዳይነሳ ታግዶ የቆየው። ባሳለፍነው ቅዳሜ ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ለ3 ወራት ያህል ከመሬት እንዳይነሳ በመላው ዓለም ታግዶ የቆየውን ድሪም ላይነር አውሮፕላን ማብረሩ ተዘግቧል። ለመሆኑ አየር መንገዱ ሰዎችን ጭኖ ከዓለም በቀዳሚነት መደበኛ በረራውን ለማካሄድ ምን አነሳሳው? በረራውስ በምን መልኩ ነበር የተጠናቀቀው? ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የበረራ መምሪያ ኃላፊ፥ ካፒቴን ደስታ ዘርዑን አነጋግሬያቸው ነበር፤ የሚከተለውን መልስ በመስጠት ይንደረደራሉ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ