1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሬናሞ ዕጣ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 26 2010

የምዕራቡን ቀኝ ዘመም የፖለቲካ መርሕ የሚያቀነቅኑት ድላካማ ከቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ የነጭ ዘረኛ መንግስት እና ከምዕራባዉያን በሚያገኙት ድጋፍ በስልጣን ላይ የሚገኘዉን ፍሬሊሞ የተሰኘዉን ኮሚንስታዊ ፓርቲ እና መንግስት ለረጅም ዓመታት ሲወጉ ነበር።

https://p.dw.com/p/2xBoG
Mosambik  Afonso Dhlakama
ምስል Getty Images/S. Costa

(Beri.Berlin) Dhlakama ist tot - MP3-Stereo

የሞዛምቢክን አንጋፋ የነፃነት ተፋላሚ ድርጅት ሬናሞን ለረጅም ጊዜ የመሩት አልፎንሶ ድላካማ ሞቱ።65 ዓመታቸዉ ነበር።አንጋፋዉ የነፍጥ ተዋጊ ቡድን መሪ አሟሟታቸዉ በድንገተኛ የልብ ሕመም ከሚል ግምት በስተቀር ትክክለኛዉ ምክንያት አልታወቀም።የምዕራቡን ቀኝ ዘመም የፖለቲካ መርሕ የሚያቀነቅኑት ድላካማ ከቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ የነጭ ዘረኛ መንግስት እና ከምዕራባዉያን በሚያገኙት ድጋፍ በስልጣን ላይ የሚገኘዉን ፍሬሊሞ የተሰኘዉን ኮሚንስታዊ ፓርቲ እና መንግስት ለረጅም ዓመታት ሲወጉ ነበር።ሁለቱ ቡድናት የሠላም ዉል ከተፈራረሙ በኋላም ወደ ተቃዋሚ ፓርቲነት የተቀየረዉን ፓርቲያቸዉን ሲመሩ ነበር።ከሰወስት ዓመት በፊት ስምምነቱ ፈርሶ ሬናሞ ተመልሶ የነፍጥ ዉጊያ ጀምሮም ነበር።የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት የድላካማ ሞት ለሞዛቢክ ሠላም ጠቃሚም ጎጂም ሊሆን ይችላል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ