ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ የኤች አይ ቪ ተሐዋሲን ስርጭትን ለመቀነስ በተለያዩ አካላት ርብርብ በተከታታይ ለዓመታት በተደረገዉ ጥረት ከፍተኛ ለዉጥ መመዝገቡን ብዙዎች ያምኑበታል። ካለፉት አራት እና አምስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ምንም እንኳን የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ቢጨምርም አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ እየተነገረ ነዉ። ለዚህ ምክንያቱም ከምንም በላይ የተገኘዉ ዉጤት ያስከተለዉ መዘናጋት መኖሩን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያነሳሉ። የዶቼ ቬለ ሳምንታዊ የጤና እና አካባቢ መሰናዶ ሰፋ ያለ ዉይይት በዚህ ላይ አካሂዶ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት አስደምጧል። ክፍል አንድ ባለፈዉ ሳምንት ቀርቧል። የዉይይቱን ክፍል ሁለት ሙሉ ቅንብር ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ