ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 4 2009ማስታወቂያ
UNAIDS እንደሚለዉ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም ወዲህ አዲስ በተሐዋሲዉ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ብዙም ሲቀንስ አልታየም። በየዓመቱም 1,9 ሚሊየን ገደማ ሰዎች አዲስ በኤች አይቪ መያዛቸዉን ያመለክታል። በሌላ በኩል ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ፤ አዲስ በበሽታዉ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥርም እንዲሁ እየቀነሰ መምጣቱ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል። በቅርቡ ደግሞ በተሐዋሲዉ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተነግሯል። የበሽታዉን ስርጭት ለመከላከል ይደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸዉን የሚያመላክቱ አሉ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ