ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያዉያን መከራ
ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2007የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስለጉዳዩ የሰማዉ እንደሌለ ነዉ ለዶይቼ ቬለ የገለፀዉ። ወደደቡብ አፍሪቃ ለመግባት የሚሞክሩ ኢትዮጵያዉያን ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ማኅረሰብ ሊቀመንበር አቶ ታምሩ አበበ እንደሚሉት በተደጋጋሚ ድንበር ለማለፍ ሲሞክሩ በሀገሪቱ መንግስት ኃይሎች መያዝ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዉያንም እየታገታሉ። እሳቸዉ እንደሚሉት ደቡብ አፍሪቃ የሚገቡና የገቡ ኢትዮጵያዉያን እዚያዉ ያለዉ የሀገሬዉ የዘር ጥላቻ ጥቃት ሳያንሳቸዉ በራሳቸዉ በኢትዮጵያን ሕገ ወጥ ከሀገር ሀገር ሰዉ አሸጋጋሪዎች እየታገሩ ገንዘብ ዉለዱ ይባላሉ።
እንደአቶ ታምሩ ገለፃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ወደደቡብ አፍሪቃ የሚገቡት አብዛኞቹ ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤት ንብረትና ከብቶች እየሸጡ የቋጠሯትን ለሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች በመገበር ከአፍሪቃዋ የበለፀገ ኤኮኖሚ ባለቤት የማንዴላ ሀገር ገንዘብ ለመዛቅ የተመኙ የዋሆች ናቸዉ። በዛሬዉ ዕለት እንኳን ከእስርመፈታታቸዉየተነገራቸዉ30 ሰዎች በሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ ማላዊ ድረስ ተሸኝተዉ የድንበር አጥር በጥሰዉ ሲገቡ በመንግሥት ጠባቂዎች እጅ የገቡ ነበሩ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ቤት የጀመረዉ ሕገወጥ አሸጋጋሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ርምጃ ወደሌሎች አካባቢዎችም ሰንሰለቱን ተከትሎ ቢቀጥል የብዙዎችን ሕይወት ከአደጋ ለማዳን እንደሚችልም አቶ ታምሩ አመልክተዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ