ደቡብ ሱዳን እና የሰላም ተስፋዋ
እሑድ፣ ሐምሌ 3 2003ማስታወቂያ
የሕዝቧ የነጻነት ምኞት በዛሬው ዕለት እውን ሆኖዋል፤ በነዳጅ ዘይት ሀብት የታደለችው፡ ግን በጦርነት የተዳቀቀችው ደቡብ ሱዳን የሀገር ግንባታውን ተግባር ከሕዝቧ ጋ ባንድነት በመሆን አንድ ብላ መጀመር ይኖርባታል። ከሰሜን ሱዳንም ጋ ያላትን ልዩነት ማብቃት ይጠበቅባታል። ግን ጥያቄው ዛሬ በይፋ የተረጋገጠው የደቡብ ሱዳ ነጻነት ሕዝብዋ የታገለለትን እና ከብዙ ጊዜ ወዲህ ሲጠብቀው የቆየውን፡ ማለትም፡ በሀገሩ በሰላም የመኖር ተስፋውን ገሀድ ያደርግለት ይሆን? የተሰኘው ነው።
ሊና ሆፍማን
አርያም ተክሌ
መስፍን መኮንን