ደቡብ ሱዳን እና ህጻናት ወታደሮቿ
ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2008ማስታወቂያ
የተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በደቡብ ሱዳን እንደገና ባገረሸው ግጭት ምክንያት ህፃናት ለውትድርና መመልመላቸው እንዳሳሰበው በቅርቡ አስታውቋል ። በጎርጎሮሳዊው 2015 ፣ 1775 የቀድሞ ህጻናት ወታደሮች በዩኒሴፍ ታዛቢነት ከውትድርና ቢሰናበቱም እንደ አዲስ በተጀመረው ውጊያ ምክንያት ግን ይህ ሁለ መና ሊቀር እንደሚችል አሳስቧል ። ያኔ አብዛኛዎቹ የተለቀቁት የደቡብ ሱዳን ዴሞክራሲያዊ ጦር ከተባለው ቡድን ነበር ። ዩኒሴፍ እንደሚለው በጎርጎሮሳዊው 2016፣ 206 ህጻናት ከተዋጊ ቡድኖች ጋር ተሰልፈው እንዲዋጉ ተመልምለዋል ። ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአሁኑ ጊዜ ህጻናትን ለewteድርና ከሚመለምሉት ወገኖች መካከል መንግሥትም ይገኝበታል ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል ። በዚሁ ጉዳይ ላይ የናይሮቢውን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዋል።
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ