ደቡብ ሱዳንና መልክአ-ምድሯ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 9 2005ከሚገኘው BEUTH ከፍተኛ የቴክኒክ ተቋም ጋር በመተባበር፤ የራሷን መልክአ-ምድራዊ ካርታ አቅድ ባለው ሁኔታ ለማሰናዳት ተዘጋጅታለች። ዩታ ሽቬንግስቢር ያሰናዳችውን ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።
ትንንሾቹ የጭቃ ቤቶች ከጎናቸው በተሠራ ሰማያዊ ቀለም ባለው ረጅም ህንጻ ተውጠዋል። የቻይናና የማሌሺያ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች፤ በላዕላይ ነጨ ዐባይ ደፍድፍ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አውታሮች ተክለዋል፤ ቧንቧዎችንም ዘርግተዋል። ይሁንና የአካባቢው ህዝብ ገና የዚህ የተፈጥሮ ሀብት ትሩፋት ተቋዳሽ አልሆነም። ደቡብ ሱዳን ያላት የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት መጠን የአፈርና ቋጥኝ ተመራማሪ ጆሰፍ ሌጎ ጀምስ እንደሚሉት ገና አልታወቀም።
«ነጻ እንደወጣን፤ ማንኛውም መረጃ በሰሜን ሱዳናና ከዚያ ውጭ እንጂ፣ በእኛ እጅ አልነበረም። መረጃው ተነፍጎን ነበር።ለትምህርት ወደ ውጭ የሚሄድ ሰው፤ ብዙ መረጃ በዚያ እንደሚገኝ ይገነዘባል፤ ግን አያገኘውም። መግዛት ይኖርበታል። እኔ ራሴ አሁን እንደ ደቡብ ሱዳናዊ የአፈርና ቋጥኝ ባለሙያ ራሴ ነኝ ካርታውን በአዲስ መልክ ማዘጋጀት የሚኖርብኝ።»
ጆሰፍ ጄምስ፤ የደቡብ ሱዳንን የተፈጥሮ ሀብት በአቅድ በማጥናትና በማመላከት ረገድ ከቀደምት የአገሪቱ ጠበብት አንዱ ናቸው። የበርሊኑ BEUTH የሥነ ቴክኒክ ከፍተኛ ተቋም ሥልጠና ከሰጣቸው በኋላ እርሳቸውና ሌሎች የጁባ ዩንቨርስቲ ባልደረቦቻቸው አሁን በሥርዓት የመልክአ-ምድራዊ ሰነድ ለማዘጋጀት ተሠማርተዋል።
3,ATMO (የስልጠና ትምህርት)
ለልምምድ፣ ተሳታፊዎቹ፤ ከሳቴላይት የአቅጣጫ መጠቆሚያ ንዑስ መሣሪያ ተሰጥቶአቸው ያን በአጅ ይዘው፤ በዛ ላሉ ሰዓቶች፤ በጁባ በህንጻዎችና በጎዳናዎች ማዕዘን ያለውን ርቀትና ትክክለኛ አቀማመጥ ይለካሉ። በመጨረሻም በመለካት ያገኙአቸውን ውጤቶች በአጠቃላይ ኮምፑዩተር ውስጥ እንዲመዘገቡ ያደርጋሉ።
ፕሮፌሰር Bernd Meissner በጀርመንና በ 4 የአፍሪቃ ሃገራት ዩንቨርስቲዎች፣የሳይንስ ፕሮጀክቶች አሏቸው።
4,«በሚመጡት 2 ዓመታት የጁባን የከተማ ካርታ አሰናድተን ለማቅረብ ነው የምንሻው።
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ