ደራሲ መሥፍን ተቀበረ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 8 2006ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊዉ ደራሲ፤ሐያሲና መምሕር መሥፍን ሐብተማርያም ዛሬ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ዉስጥ ተቀበረ።መስፍን ሐብተማርያም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የወግ ፀሐፊ ነበር።በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ወጎችን የፃፈና ያሳተመ፤ ተርጓሚ፤ የሥነ-ፅሁፍ ሐያሲ እና አዲስ አበባና አሥመራ ዩኒቭርስቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ያስተማረ የሥነ-ፅሁፍ ሰዉ ነበር።መሥፍን በሕክምና ሲርዳ ቆይቶ ባለፈዉ ዕሁድ ነዉ ያረፈዉ።69 ዓመቱ ነበር።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት ተከታትሎት ነበር።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ