1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደሞዝ ስላልተከፈላቸው የትግራይ ክልል ሠራተኞች የመንግሥት ምላሽ

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 4 2013

ትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች አሁን ባለው ጦርነት ምክንያት ክፍያቸውን እያገኙ አይደለም። ሆኖም አዲስ አበባ የሚገኙና ወደ ከተማው የመጡት የጡረታ ተጠቃሚዎች ማስረጃዎቻቸውን እየያዙ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ አሠራር መዘርጋቱን በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተናግሯል።

https://p.dw.com/p/407nA
Äthiopien Tigray-Provinz Straße in Mekele | ARCHIV
ምስል Maggie Fick/REUTERS

«በአሁኑ ጌዜ በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት መዋቅር የለውም»

በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ የማኅበራዊ ዋስትና ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች አሁን ባለው ጦርነት ምክንያት ክፍያቸውን እያገኙ አይደለም። ሆኖም አዲስ አበባ የሚገኙ እና ወደ ከተማው የመጡት የጡረታ ተጠቃሚዎች ማስረጃዎቻቸውን እየያዙ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ አሠራር መዘርጋቱን በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አንድ ባለሞያ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የሰላም ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ጌዜ በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት መዋቅር የለውም ብሏል። በትግራይ ክልል ከሁለት መቶ ሺህ በላይ የክልል እና የፌዴራል ሠራተኛ የነበሩ ነዋሪዎች እንዲሁም ጡረተኞች ለወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው በመግለጥ አማረዋል።


ሰለሞን ሙጬ


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ