ደም እና ባሕሪያቱ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2008ብዙ ደም እንዳይፈሰን ፍሰቱ የሚገታበትን ቅመም አመንጪዉም ይኸዉ ደም ነዉ። በሰዉነታችን ዉስጥ የሚገኘዉን ቆሻሻ ወደኩላሊት እና ጉበት አምጥቶ እንዲጣራ የሚያደርገዉ ደም ነዉ። ከዚህም ሌላ የሰዉነታችንን ሙቀት ሚዛናዊ አድርጎ የመቆጣጠር ኃላፊነቱም የእሱ ነዉ። አንድ ሰዉ በሰዉነቱ ዉስጥ የሚኖረዉ የደም መጠን እንደክብደቱ እና ርዝመቱ ይለያያል። በአማካይ ግን በአዋቂ ዕድሜ ደረጃ የሚገኝ ወንድ 5 ሊትር ደም እንዳለዉ እና በተመሳሳይ ዕድሜ እንዲሁም የሰዉነት ክብረትና ርዝመት ያላት ሴት ደግሞ 4 ,5 ሊትር እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ ልዩነት ከምን መጣ የሚለዉን የዉስጥ ደዌ እና የደም በሽታዎች ልዩ ሃኪም ዶክተር ፍሰሃጽዮን ታደሰ በዝርዝር አብራርተዉታል።
በቂ የብረት ወይም አይረን ንጥረነገር ያላቸዉን መግቦች በተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓት በመዉሰድ ደምን ቶሎ መተካት ይቻላል ቢባልም ግን ዶክተር ፍሰሀጽዮን እንዳሉት ቶሎ ቶሎ ግን ደምን መሰጠት አይቻላም። አንድ ጤናማ ሰዉ በዓመት አራት ጊዜ ብቻ በሦስት ወራት ልዩነት ነዉ ደም መለገሥ የሚችለዉ። ይህ የሚደረገዉ በቂ የብረት ክምችት በሰዉነቱ እንዲኖር ነዉ። የደም ማነስ የሚባለዉ የጤና ችግር መንስኤ የብረት እጥረት መሆኑን የሚያስረዱት የዉስጥ ደዌ እና የደም በሽታዎች ልዩ ባለሙያ ብረት ወይም አይረንን ይብዛም ይነስ ከሁሉም የምግብ ዓይነት ማግኘት እንደሚቻል ነዉ የሚናገሩት።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ