1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደመወዝ ጭማሪ፤ የኑሮ ውድነትና የኤኮኖሚ ይዞታ

እሑድ፣ ነሐሴ 11 2006

በአፍሪቃው ክፍለ-ዓለም ፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት በማሳየት ላይ መሆናቸው ከሚነገርላቸው ጥቂት ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። እ ጎ አ እስከ 2020 ባለ ማዕከላዊ ገቢ ሀገር ለመሆን እቅድ እንዳላት የምትገልጸውና «ይህን ትልም የማሳካት

https://p.dw.com/p/1CvZs
ምስል picture alliance/kpa

አቅም አላት» ሲል የዓለም ባንክ የተናገረላት ኢትዮጵያ፣ ከ 2003 ዓ ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቁጥራቸው ከ 1,3 ሚሊዮን ለማያንሱት የመንግሥት ሠራተኞች ፣ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ጠ/ሚንስትሩ ባለፈው ሰኔ 16 ,2006 ዓ ም፣ ይፋ ካደረጉና ዘግየት ብሎም በገንዘብና የኤኮኖሚ ልማት ሚንስቴር፣ እንዲሁም የሲቭል አገልግሎት መሥሪያ ቤት ጭማሪው ከ33%-46% እንደሚዘልቅ ካሳወቁ ወዲህ፣ ጉዳዩ ዐቢይ የመነጋገሪያ ርእስ ሆኖ መቀጠሉ የታወቀ ነው።

ከጭማሪው ሠናይ ዜና ጋር ተያይዞ የዋጋ መናር መቅኖ ያሳጣዋል ከሚለው ሥጋት ጋር ፤ ለደመወዝ ማስተካከያው፣ በዓመታዊው በጀት ላይ 10,3 ቢሊዮን ብር ይጨመራል መባሉ፣ የገንዘብና የኤኮኖሚ ጠበብት የተለያዩ ሐሳቦችን እንዲያንጸባርቁ መጋበዙም አልቀረም።

ስለ ደመወዝ ማስተካከያውና የሀገሪቱ የኤኮኖሚ አቅም፣ ባለሙያዎች ምን ይላሉ? ዶቸ ቨለ ለዚህ ሳምንት የመረጠው የውይይት ርእስ ነው።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ