1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያባትዋ ልጅ

ነጋሽ መሐመድ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 2 2009

የመጀመሪያ መፅሀፏን «ባርቾ» ብላዋለች ።ሁለተኛዉን «በቅርብ ቀን» ብላናለች። ከዚህም ሌላ በተለይ በማሕባራዊ መገናኛ ዘዴ ተሳትፎዋ በይበልጥ በፌስቡክ ጽሑፎቿ ትታወቃለች።

https://p.dw.com/p/2U2LX
Buchcover Baricho amharisch
ምስል Hiwot Emshaw

NM - MP3-Stereo

ሁለተኛ ደረጃን ኮኮበ ፅባሕ ትምሕርት ቤት ተማረች።አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አጠናች።«ጥሩ» ያለችዉን ሥራ ያዘች።እና ትፅፍ ገባች።የመጀመሪያ መፅሐፍዋ ለሰወስተኛ ጊዜ ታትሟል።ርዕሱን «ባርቾ» ብላዋለች። ሁለተኛዉን «በቅርብ ቀን» ብላናለች። ከቀዳሚዉም፤ ከሚጠበቀዉም የቀደሙት ግን የማሕባራዊ መገናኛ ዘዴ ፅሁፎችዋ ናቸዉ።የፌስቡክ።

«አዙሪቱና የዞረብን እኛ» ይላል -መስከረም ማብቂያ የለጠፈችዉ ግጥም መሰል መጣጥፍ።ሕይወት እምሻዉ የዛሬ እንግዳችን ናት።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ