ያለፍርድ የታሠረዉ ጋዜጠኛ
ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2008ማስታወቂያ
ነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ የሠማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ክስ ሳይመሰረትበት ከአራት ወራት በላይ መታሠሩን ጠበቃዉ አስታወቁ።ጠበቃ አመሐ መኮንንን ዛሬ እንዳስታወቁት የሐገሪቱ የፀረ-ሽብር አዋጅ በሚያዘዉ መሠረት ፖሊስ በደንበኛቸዉ ላይ በአራት ወራት ዉስጥ ክስ መመሥረት አለያም እስረኛዉን መልቀቅ ነበረበት።ፖሊስ በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም እስካሁን በይፋ ክስ አልመሰረተም ጋዜጠኛ ጌታቸዉን አለቀቀምም።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ