1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ እና የስለላ ቅሌት

ሰኞ፣ ሰኔ 3 2005

ዋሽንግተን ፖስት እና ዘ ጋርዲያን የተባሉት የአሜሪካውያን እና የብሪታንያውያን ጋዜጦች ባለፈው ሐሙስ ያወጡት ዘገባ ይፋ እንዳደረገው፣ በዩኤስ አሜሪካ «ብሔራዊ የፀጥታ ወኪል» በብዙ ቢልዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የስልክ ደንበኞችን ካለፉት አሥር ዓመታት በላይ ወዲህ በመሰለል ላይ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/18nDg
ምስል Reuters/Ewen MacAskill/The Guardian/Handout
NSA-Zentrale in Maryland
ምስል picture-alliance/dpa

መሥሪያ ቤቱ «ፕሪዝም» በተሰኘ ፕሮግራም አማካኝነት ጉግል፤ አፕል እና ፌስቡክ፣ የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት ኮምፒውተር መረጃዎች ዋና ማከማቺያ፣ ማለትም፣ ሰርቨሮችን በመሰለል የግለሰቦች እንቅስቃሴን እንደተከታተለ ነው የጋዜጦቹ ዘገባ ያስታወቀው። ይህን በሚስጥር የተያዘውን ዜና ለጋዜጦቹ የሰጠው ግለሰብ አንድ የ 29 ዓመት የቀድሞ የሲ አይ ኤ ሰራተኛ አሜሪካዊ መሆኑ ተሰምቶዋል። ስለ ግለሰቡ ማንነት እና ስላጋለጠው ሚስጥር በትክክል የሚታወቀውን እንዲነግረን የዋሽንግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን ቀደም ሲል በስልክ ጠይቄው ነበር።


አበበ ፈለቀ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ