«ዩኔስኮ» ፍቼ ጨምባላላን መዘገበ
ሐሙስ፣ ኅዳር 23 2008ማስታወቂያ
ድርጅቱ ዊንድ ሆክ ናሚቢያ ላይ ባካሄደዉ አስረኛዉ ጉባኤ የኢትዮጵያዉን ይህን ባህላዊ እሴት ጨምሮ፤ የሌሎች የ11 ሃገራትን በጥቅሉ 15 ባህላዊ እሴቶችን በማይዳሰሱ ባህላዊ ሀብቶች ዝርዝር ዉስጥ ማስገባቱን ታዉቋል። ፍቼ ጫምባላላ ለሁለት ሳምንታት በተከታታይ የሚከበር የሲዳማ ህብረተሰብ የአዲስ ዓመት በላይ ሲሆን በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የጎሳዉ የሀገር ሽማግሌዎች እና መሪዎች ለማህበረሰቡ እና ለተተኪዉ ትዉልድ ስለ ሥራ ክቡርነት ፣ መልካም አስተዳደርን እና ተግባብቶ፤ ተከባብሮ አብሮ መኖርን የሚያስተምሩበት መድረክ መሆኑን የ«ዩኔስኮ» ጋዜጣዊ መግለጫ ዘርዝሯል። ሸዋዬ ለገሠ በድርጅቱ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑትን ፕሮፌሰር ምትኩ ኃይለን በአጭሩ አነጋግራለች።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ