የFAO የምግብ እጥረት ዘገባ
ሐሙስ፣ መስከረም 6 2003ማስታወቂያ
እንዲያም ሆኖ በዓለም የተፈጠረዉን የፋይናንስና የኤኮኖሚ ቀዉስ ተከትሎ በቂ ምግብ የሚያስፈልገዉ ህዝብ ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን እንደሚልቅ ጠቁሟል። የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አሁን ክፉና የሚያጠቃዉ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ አገራትን ሲሆን። ሁለት ሶትተኛዉ ቁጥር በሰባት አገራት ይገኛል። እነሱም ባንግላዴሽ፤ ቻይና፤ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፤ ኢትዮጵያ፤ ህንድ፤ ኢንዶኔዢያና ፓኪስታን መሆናቸዉን የFAO ዘገባ ያስረዳል። ድርጅቱ በዘገባዉ እንዳመለከተዉ በየስድስት ሰከንዱ አንድ ህፃን ከርሃብ ጋ በተገናኘ በሽታ ምክንያት ይቀጠፋል።
ተኽለእግዚ ገ/እየሱስ፤ ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ