የFAO ማስጠንቀቂያ11 ነሐሴ 2001ሰኞ፣ ነሐሴ 11 2001ዋና ጽሕፈት ቤቱ በጣሊያን ሮም የሚገኘዉ የተመ የእርሻና የምግብ ድርጅት FAO በምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት የታየዉ ዘግይቶ የመጣዉና በቂ ያልሆነዉ ዝናብ በአካባቢዉ የዉሃ እጥረትና የምርት ብልሽት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።https://p.dw.com/p/JD0iማስታወቂያ በተለይም በኬንያ፤ ኢትዮጵያና ጅቡቲ የተከሰተዉ የዉሃ እጥረት ከብት አርቢዎችና እንስሳትን ለችግር ሊዳርግ እንደሚችል ድርጅቱ አመልክቷል። በሚቀጥሉት ወራት ኤሊኖ የተባለዉ አዉሎ ነፋስ ከከባድ ዝናም ጋ ተቀላቅሎ ከመጣ ሁኔታዉ ሊለወጥ እንደሚችልም ከወዲሁ ጠቁሟል። ተኽለእግዚ ገ/ኢየሱስ /ሸዋዬ ለገሠ አርያም ተክሌ