የEBC ኃላፊዎች ሹመት
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 7 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሐገሪቱ መንግሥት የሚቆጣጠረዉን የኢትዮጵያ ማሰራጪያ ድርጅት (EBC በእንግሊዝኛ ምሕፃረ ቃሉ) ዋና ሥራ አስኪያጅና የቦርድ አባላት ሹመት አፀደቀ።እስከ ትናንት ድረስ የአማራ መስተዳድር የመገናኛ ብዙሐን ሐላፊ የነበሩት አቶ ሥዩም መኮንን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሾሙ፤ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሹመቱን አስታክኮ አስተያየቶችን አሰባስቧል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ