1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያን በማየታቸዉም ደስተኛ ናቸዉ

ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2011

ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔተር ሊምቡርግ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሶስት ቀን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንደተናገሩት በጉብኝታቸዉ ወቅት ባዩትና ከተለያዩ ወገኖች ጋር ባደረጉት ዉይይት በሐገሪቱ ያለዉን ሁኔታ ተገንዘበዋል

https://p.dw.com/p/3Fkdb
DW-Intendant Peter Limbourg  und DW-Delegation in Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky

የDW ኃላፊ ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸዉ ደስተኛ ናቸዉ

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተጀመረዉን የለዉጥ ሒደት የሐገሪቱ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በትክክል እንዲረዳዉ አዲሱ መንግሥት ለጋዜጠኞች በሩን እንዲከፍትና መረጃ እንዲሰጥ የDW ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጠየቁ።ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔተር ሊምቡርግ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሶስት ቀን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንደተናገሩት በጉብኝታቸዉ ወቅት ባዩትና ከተለያዩ ወገኖች ጋር ባደረጉት ዉይይት በሐገሪቱ ያለዉን ሁኔታ ተገንዘበዋል።ኢትዮጵያን በማያታቸዉም ደስተኛ ናቸዉ።ሊምቡርግ የመሩት የDW የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በጎንደርና በአዲስ አበባ ባደረገዉ ጉብኝት ከፖለቲከኞች፣ከጋዜጠኞችና ከመብት አቀንቃኞች ጋር ተወያይቷል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ