የ2008 ማብቂያ ክንዉኖች
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2001ማስታወቂያ
የጎርጎሳዉያኑን የዘመን ቀመር የሚከተለዉ አለም በየአመቱ እንደሚያደርገዉ ሁሉ የክርስቶስን ልደት ሊያከብር፣ የፍቅር፣ ዉዴታ፣ አክብሮት፣ዉለታዉን መጠን በሚቀበል-በሚሰጠዉ ቁስ ሊሰፍር-ሊያሰፍር ሁለት ጀምበር ቀረዉ።በሰጠ-በተቀበለዉ፣ ባወጣ ባስገባዉ እንደቦርቀ ወይ እንዳዘነ አሮጌዉን አመት ይሰናበታል።የበአል-ዝግጅቱ፣ የስጦታ ቁሱ ሸመታ እንዴትነት፤ የዘመኑ ክንዉን ምንነት ብዙ ሲባልለት ሰሞኑን ከኢራቅ እስከ አፍቃኒስታን፤እስራኤል እስከ ፍልስጤም፣ ከሶማሊያ እስከ ዚምባቡዌ፣ ከአዉሮጳ እስከ አሜሪካ የተከናወኑት ብዙ ጉዳዮች በአሉ-ሳይደርስ አከባበሩን፤ አዲሱ ዘመን ሳይበርቅ ሒደቱን በያኝ መምሰላቸዉ አጠያያቂዉ።እንዴት ለምን ላፍታ አብረን እንቆይ።