የ H1N1 ቫይረስ ስርጭት ና የዘንድሮው የሀጂና ዑምራ ጉዞ
ሰኞ፣ ሐምሌ 20 2001ማስታወቂያ
ከዚሁ ጋርም መንግስት ነፍሰ ጡሮች ህፃናት አዛውንትና አቅመ ደካሞች የዘንድሮውን የሀጂና ኡምራ ጉዞ ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉም አሳስቧል ። H1N1 የተባለው ቫይረስ በሚያስከትለው ከባድ ኢንፍሉዌንዛ የተያዘ አንድ ሰው ሳውዲ አረቢያ ውስጥ መሞቱ ዛሬ ይፋ ሆኗል ። በግል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየው ይኽው ሰው በካባዱ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሞተ የመጀመሪያው ሰው መሆኑ ነው ። በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ በዚህ በሽታ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ 300 በልጧል ። በሌላም በኩል በበሽታው ስርጭትና ቁጥጥር ላይ የተነጋገሩት የአረብ አገራት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች በዘንድሮው የሀጂና ኡምራ ጉዞ የሚሳተፉ ሰዎችን ዕድሜ ገድበዋል ። ነብዩ ሲራክ ከጀዳ--
ነብዩ ሲራክ ፣ ተክሌ የኋላ
ሒሩት መለሰ