የፕሬዝደንት ኦባማ ጉብኝት መልዕክትና ፋይዳዉ
እሑድ፣ ሐምሌ 26 2007ማስታወቂያ
የእሳቸዉ የኬንያ እና ኢትዮጵያ ጉብኝትም ሆነ በጉብኝታቸዉ ወቅት ያደረጓቸዉ ንግግሮች ግን አሁንም የበርካቶች መነጋገሪያ እንደሆኑ ነዉ። ፕሬዝደንት ኦባማ ገና ለጉብኝት እግራቸዉን ሳያነሱ ሃሳባቸዉን እንዲለዉጡ ከመጠየቅ ጀምሮ፤ የሰብዓዊ መብት ይዛታ እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ያሳስበናል ያሉ የመብት ተሟጋቾችም የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ሲያገኙ ሊያነሷቸዉ ይገባል ያሏቸዉን ነጥቦች በደብዳቤ ከትበዉ አድርሰዋቸዋል። ፕሬዝደንቱ ግን ባመዛኙ የጉብኝታቸዉ ዋና ዓላማ በሆኑ ጉዳዮች ተጠምደዉ ታይተዋል። ሳምንታዊዉ እንወያይ የጉብኝታቸዉን ፋይዳና መልዕክት ዳስሷል። ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ይከታተሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ