የፕሬዚዳንት ኦባማ ዳግመኛ ጉብኝት በበርሊን
ሰኞ፣ ሰኔ 10 2005ማስታወቂያ
ያኔ፤ ከ 200,000 የማያንስ ህዝብ ፣ በጋለ ስሜትና አድናቆት አቀባበል በማድረግ ንግግራቸው ማዳመጡ የሚታወስ ነው። ኦባማ ፤ ነገ ማታ በርሊን ገብተው ፤ በማግሥቱ በብራንደንቡርግ በር ንግግር የሚያሰሙ ሲሆን ፤ እንደያኔው ህዝቡ በጋለ ስሜት ያዳምጠቸዋል ተብሎ እንደማይታሰብ ነው የሚነገረው። ስለአሁኑ ጉብኝት ዓላማ ፣ የሁለቱ መንግሥታት መሪዎች ፣ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የጀርመን መራኀተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስለሚያተኩሩባቸው ዐበይት ጉዳዮች ፣የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ